በሸገር ሲቲ አስተዳደር ኢንቨስትመንት ቢሮ አዘጋጅነት ከሰኔ 26-28 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ኤግዚብሽን ማዕከል በተካሄደው የሽገር ኢንቨስትመንት ኤክስፖ 2026 ማለዳ ፎም በሞዴል ኤግዚቢተር
እና በስራ ዕድል ፈጠራ በ2018 ባስመዘገቡት የላቀ አፈጻጸም በዕለቱ የሁለት ዋንጫዎች እና ከሶስት በላይ የእውቅና ሰርተፊኬት ተሸላሚ በመሆን በድምቀት አጠናቋል።
በኤክስፖ ላይ ማለዳ ፎም ከመንግስታዊ ድርጅቶች ፣ ከማህበረሰቡ ፣ ከዓለም አቀፍ ድርጅቶች ለተወከሉ ጎብኚዎች እንዲሁም ለአምባሳደሮች እና መሰል አካላት
ምቾትና ዘመናዊነትን ያካተቱ አዳዲስ ምርቶቹን ለእይታ ያቀረበ ሲሆን ጥልቅ ማብራሪያ እና የምርት ገለፃ አከናውኗል።
ለሶስት ተከታታይ ቀናት በኤግዚቢሽን ማዕከል በተካሄደው ኤክስፖ ላይ ማለዳ ፎም በተጨማሪነት ለተሳታፊዎች የሽልማትና የስጦታ መርሃ-ግብር አካሂዷል።